ዛሬ ማርች-8 ዓለም አቀፍ የሴቶችን ቀን ስናከብር በመላው ዓለም ላሉ ሁሉ በአንድነት ሁላችን ግድ እንደምንል በማሳየት ነው። የዘንድሮው ዓለም አቀፍ የሴቶች ቀን “ለሁሉም ሴቶች እና ልጃገረዶች መብት ፣ እኩልነት እና ልህቀት” በሚል መሪ ሀሳብ እየተከበረ ይገኛል።
ጭላንጭል በእዚህ ቀን የአፍሮ ፌሚኒዝም አቀንቃኞችን፣ ደጋፊዎችን ፣ የሚዲያ እና የሲቪል ማህበረሰቡን ፣ ወጣቶች እና የማህበረሰብ መሪዎችን ለጋራ ለውጥ እና ትግል ጥሪዋን ታቀርባለች።ጭላንጭል በወል ጥላቻ እና መድሎ የተገፉ እና ትኩረት የተነፈጋቸው የLBQT ሴቶች መብቶች እና የፆታ እኩልነት እንዲከበሩ መታገል እና የለውጥ እርምጃዎች እንዲወሰዱ መጠየቅ ከመቼውም ጊዜ በላይ አስፈላጊ መሆኑን ታምናለች። በእዚህም መሪዎቻችን ለሁሉም ሴቶች መብት መከበር እና ለፆታ እኩልነት የተሻሉ እርምጃዎች እና የፖሊሲ ለውጦች ላይ ኢንቨስት እንዲያደርጉ እንጠይቃለን!
በጋራ ድምፃችንን በማጉላት እና በመወያየት የተሻለ እና ትርጉም ያለው ለውጥ ማምጣት እንደምንችል እናምናለን!!
ለሴቶች መብት መከበር እና ለተሻለ ማህበራዊ ለውጥ በጋራ እንቁም!!! ብሩህ ተስፋን ለሁለም እናረጋግጥ!
ጭላንጭል