ጾታ እና ስነ ተዋልዶ ሁለት የተለያዩ ነገር ግን ተዛማጅነት ያላቸው ቃላት ናቸው፤ እነዚህም ቃላት ወሳኝ እና ጥልቀት ያለው ትርጉም ሲኖራቸው አንድ አይነት ትርጉም ያላቸው ወይም እርስ በርስ ተለዋዋጭ ግን አይደሉም። ጾታ እና/ወይም ስነ-ወሲብ እንዲያው በጥቅሉ ሰፊ ወይም አቃፊ ቃላቶች ቢሆኑም በዉስጣቸዉ የ አንድን ሰው ጾታዊ ስያሜ እና የ ፍቅር ጓደኛ ምርጫን ያጠቃልላሉ። ስነ ተዋልዶ ግን ወሲብን ባካተቱ እና/ወይም ባላካተቱ መንገዶች ልጅ ስለመዉለድና ህይወትን ስለማስቀጠል ብቻ ያጠነጥናል።
የ ጾታ እና ስነ ተዋልዶ ጤና እንደ ማንኛዉም የጤና ዘርፍ እኩል እና አስፈላጊ ነው።
የ ‘’ጾታ እና ስነ ተዋልዶ ጤና መብት’’ ማለት አንድ ግለሰብ በሙሉ ጤናው እና በተክለ ሰዉነቱ የተጠበቀ እንዲሆን የሚያገኘው፣ ራስ በራስ የመወሰን መብት (ራስ ገዝነት) የጤና ትምህርትና የጤና አገልግሎት የማግኘት መብት፤ እንዲሁም በነጻነት የወሲብ አጋር መምረጥ ፤ ራስን በግብረ ስጋ ግንግኙነት ከሚመጡ በሽታዎች እና ካላስፈላጊ እርግዝና መከላከል የሚችልባቸው መንገዶች የማመቻቸት መብት እና የውሳኔውን ብቸኛ ባለቤትነት የሚያረጋግጥበት ነው።
ሰዎች የጾታዊ እና የስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎቶችን ሲያገኙ ከሥነ ተዋልዶ ሥርዓት ጋር በተዛመደ የሚሰጥ የሕክምና እንክብካቤ ለምሳሌ በግብረ ሥጋ ግንኙነት የሚተላለፉ በሽታዎችን ማከም፣ ወይም የወሊድ መከላከያ እና የጽንስ ማቋረጥ እንክብካቤን መስጠት የመሳሰሉትን በራስ ከመወሰን ጋር አጣምሮ ይህንን አይነት መብት መጠየቅ እንዲችሉ ያደርጋቸዋል።
በተጨማሪም የጾታዊ እና የስነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት የጾታ ትምህርትን ማግኘት፣ ደህንነቱ የተጠበቀ፣ ውጤታማ፣ ተመጣጣኝ እና ተቀባይነት ያለው የወሊድ መቆጣጠሪያ ዘዴዎችን እንዲሁም ተገቢውን የጤና እንክብካቤ አገልግሎት ማግኘትን ያጠቃልላል። ሴቶች በእርግዝና እና በወሊድ ጊዜ በሰላም ማለፍ መቻላቸው ጥንዶች ጤናማ ልጅ የመውለድ ጥሩ እድል ሊሰጣቸው ይችላል።
ግለሰቦች የጾታ እና ሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎት ፍትሃዊነት በእኩልነት አያገኙም። በእኩልነት ማግኘት የተሳናቸውም በማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ የኑሮ ደረጃ፣ የትምህርት ደረጃ፣ ዕድሜ፣ ጎሳ፣ ሀይማኖትና በአካባቢያቸው በሚገኙ ሃብቶች ላይ መሰረት ያደረገ ተጽዕኖ ስላለባቸው ነው። በተጨማሪም የግለሰቦች የወሲብ ዝንባሌዎች እና ምርጫዎች የሥነ ተዋልዶ ጤና አገልግሎቶችን የማግኘት መብት፣ ተደራሽነት እና ጥራት ላይ ልዩነት እንዲገን ተጽዕኖ ስለሚያሳድር በተለይም በLGBTQ+ ማህበረሰብ ውስጥ ተጽዕኖዎች ገነው ይታያሉ።
ጥንዶች/የወሲብ አጋሮች የግብረ ሥጋ ግንኙነትን ለመራባት መፈለጋቸውን በራሳቸው መምረጥ ይችላሉ፣ እንዲሁ ልጅ ያለመውለድ መብታቸው የተጠበቀ ነው።
በማደግ ላይ ባሉ ሀገራት ያሉ የLGBTQ+ ማህበረሰቦች የጾታዊ እና የስነ ተዋልዶ ጤና አጠባበቅ አገልግሎት የተነፈጉ ሲሆን በሚያስከትለው መዘዝም በዋናነት አካላዊ (በጾታዊ ግንኙነት የሚተላለፉ ኢንፌክሽኖች፣ ኤችአይቪ፣ ፊስቱላ፣ ሄሞሮይድስ ወዘተ) እና ስነ ልቦናዊ (ድብርት፣ የወሲብ ብስጭት፣ ጭንቀት፣ ሱስ የሚያስይዝ መታወክ ወዘተ) እየተሰቃዩ አሉ።
ጾታን የመቀየር ቀዶ ጥገና እና የመራባት ህክምና ሌላው በጣም አስፈላጊ የSRH አንዱ ገጽታ ነው። የLGBTQ+ ማህበረሰብ አባላት ለወሲብ መልሶ መመደብ ቀዶ ጥገና እድል ሊያገኙ እና የመራቢያ መብቶቻቸውን በወሊድ ክሊኒክ ውስጥ ሰርሮጋሲ፣ በብልቃጥ ማዳበሪያ እና በአንድ ሰው አካላዊ እና ስነ ልቦናዊ ማህበራዊ ጤና ላይ ወሳኝ ሚና የሚጫወቱትን ጉዲፈቻ ማግኘት መቻል አለባቸው።